=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እያንዳንዷ እስትንፋሳችን አየር ወደ ውስጥ ማስገባትና ማስወጣትን የያዘ ሲሆን አንዱ ሌላውን ያለ ማቆም ይከተላል። ይህ ሂደት በተፈጥሮ ያለኛ ቁጥጥር ወይም ንቃተ ህሊና ይፈጠራል። እያንዳንዷ እስትንፋሳችነም በህይወት ለመቆየት ምክኒያት ነው። በእያንዳንዷ እስትንፋሳችነም ህይወታችን ይራዘማል።
ነገርግን ይህ አንድ ቀን ያቆማል። ያኔ የመጨረሻ እስትንፋሳችን ላይ ቀልባችን በምን ሁኔታ ላይ ይሆን? በዚህ መጽሐፍ ኡስማን ኑሪ ቶፕባሽ ለሞት የመዘጋጀትን አስፈላጊነት ይጠቁመናል። እያንዳንዱ ህይወት ያለው ፍጡር በሙሉ ይሞታል። ይሁን እንጅ ሁሉም ህይወት ያላቸው ፍጡራኖች ለዚህ ለመጨረሻ እስትንፋስ በመዘጋጀት ህይወታቸውን አያሳልፉም።
እስልምና ሁሉም የሰው ልጆች እና አጋንት ቀጥተኛውን መንገድ ይከተሉ ዘንድ ይጣራል። ሁላቸውም ዘር ፣ የቆዳ ቀለም ፣ ፆታ ፣ ብሄር ሳይለያቸው ሙስሊም መሆን ይችላሉ። እስልምና የሰው ልጆችን የሚከፍላቸው በሃላፊነታቸው እና በመብታቸው ሲሆን ሁለት የሰው ልጆች አሉ። እነሱም አማኝ እና ከሃዲ ናቸው።
ይህ መጽሐፍ የኢስላምን ሁለንተናዊ ገፅታ ለመረዳት መልካም አስተዋፅኦ የሚኖረው ሲሆን ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ላልሆኑትም ወገኖች ጠቀሜታው ጉልህ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።
ከኢማን በረከት ትልቁ ፍሬ ፍጡራኖችን በእዝነት አይን መመልከት እና ሁሉንም ፍጡራን በውዴታና በፍቅር መቅረብ ነው። ይህ የሰው ልጆችን ህይወት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን ወደ እዝነት እና ይቅር ባይነት ግዛት ያዘምታል። ያኔ ለሁሉም ፍጡራኖች ፍቅርና እዝነት ይኖረዋል።
በዚህ አለም ሰው የመሆን ባህሪ መለያ ሲሆን በልባችን ከጌታችን ጋር ያለንን ግኑኝነት የምናጠነክርበት ነው። ሙእሚን ሰው ሁልጊዜም በእያንዳንዱ ጥረትና ትግሉ የሌሎች ሰዎች ልብ ላይ ሰላም ያለው ነው።
ኢስላም የእዝነት ሃይምኖት ሲሆን እዝነቱ ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ የሰው ልጆች ፣ ከሰው ልጆችም አልፎ ለእንስሳት ጭምር ነው።
የኢስላም አብይ ስብዕና የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ዋነኛ መገለጫቸው አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው እዝነት ነው። ዛሬ ግን የሰው ልጅ እርስ በርሱ በመጨካከን እና በመበላላት ከአውሬዎች እንኳ በልጦ በተገኘበት በዚህ ዘመን የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእዝነት ትምህርትና ምሳሌ ከአየርና ከውሃ የበለጠ እጅጉን ይልስፈልገዋል።
እምነት የአእምሮ ብርሃን ነው። የህሊና መወልወያ መሳሪያ ነው። ልብን ማለስለሻ ቅባት ነው። አላፊና ጠፊ ከሆነችው ከዚህችኛዋ አለም ወደ ቀጣዩ አለም በስኬትና በደስታ ለመጎዝ ልባዊ እምነት ወሳኝ ነው። የእምነት ብርሃን የተነፈገች ነፍስ መጨረሻዋ ውርደት ነው።
የሰው ልጅ በምድር ላይ ህልውና አግኝተው መኖር ከጀመሩ አንስቶ ያለ እምነት እንዳይባዝኑና እንዳይዋትቱ መለኮታዊ አመራርና ነብያት በየዘመናቱ ሲላኩላቸው ቆይተዋል። የአሏህ ወዳዶች በእነዚህ ሁለት መመሪያዎች እየታገዙ የህይወታቸውን ቅኝት ሲያስተካክሉና ሲመላለሱ ኖረዋል። እምነት ሲባል ከመለኮት የሚሰጥ የሆነ ምርጥ ፀጋ ነው።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|