XtGem Forum catalog
free book gift
Iqra Iqra Note

50 መሠረታዊ የተውሂድ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

free book gift

ተውሂድ የእስልምና ሃይማኖት መሰረት ሲሆን በአሏህ እና በፍጡራኖቹ መካከል የሚኖረውን ግኑኝነት ግልፅና ጉልህ ያደርጋል። ይህም በአሏህ አንድነት ፣ ተንከባካቢነት ፣ የፍጥረተ አለም ገዥ መሆኑን እና ማንኛውም የአምልኮት ተግባር ለእሱ ብቻ የሚገባ መሆኑን ማመንና መቀበል ይጠይቃል።

የዚች መጽሐፍ አላማ መሠረታዊ የተውሂድ ፅንሰሃሳቦችን በጥያቄና መልስ መልክ ማስጨበጥ ሲሆን 50 ያህል ጥያቄዎችንና መልሶቻውቸን አካታለች። የቀረቡት ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ፤ መልሶቹ ደግሞ አጭር ግን አጥጋቢ እንዲሆኑ የሚቻለውን ሁሉ ተደርጎል። መጽሐፏ በየትኛውም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ጠቀሜታ እንደሚኖራት ይታመናል።

Youth-Mission Iqra

የእምነት መሠረቶች ትንታኔ
(አርካኑል ኢማን)

free book gift

በዚህ መጽሐፍ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን ስለተውሂድና አስፈላጊነቱ ፣ ስለ እስልምና ሃይማኖት ፣ ስለ እስልምና ማዕዘናት ፣ የእስልምና አቂዳ መሰረቶች የሚሉ አርዕስቶች በሰፊው ተዳሰውበታል። ስለ እስልምና ሃይማኖት ከመሠረቱ ቀለል ባለመልኩ ለመረዳትና ለማወቅ ጥሩ መጽሐፍ ነው። ሃይምኖቱን ከመሰረቱ ለመረዳት የሚሻ ሰው ይችን መጽሐፍ ያንብብ።

Youth-Mission Iqra

የአቂዳ መሰረቶች

free book gift

የእስልምና ሃይማኖት መሠረቱ አቂዳ ነው። ያለ አቂዳ ኢማን ብሎ ነገር የለም። ሆኖም አቂዳችን በቁርአን እና በሐዲስ ላይ የተመሰረተ ፣ የተስተካከለና ያማረ ካልሆነ የምንሰራው ስራ ሁሉ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። አቂዳችነን የምናስተካክለው ደግሞ በቁርአንና በሐዲስ የታዘዙትን በመስራት በመተግበር ሲሆን የተከለከሉትን በመከልከል ጭምር ነው። የሙስሊሞችም አንድነት የሚገነባውና የሚመሰረተው በአቂዳ ላይ ነው።

በዚህ መጽሐፍ ስለ አቂዳ መሰረቶች በጥያቄና መልስ መልክ ከቁርአን እና ከሱና ማስረጃዎችን በማጣቀስ ተዘጋጅቷል።

Youth-Mission Iqra

አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ

free book gift

ይች መጽሐፍ ማንኛውም ሙስሊም ጠንቅቆ ሊያውቃቸው የሚገቡ አርዕስተ ጉዳዮች እጥር ምጥን ባለ መልኩ የሚማሩባት ስትሆን አርዕስቶቹ በምዕራፍ የተከፋፈሉ ናቸው። በአጠቃላይ 18 ምዕራፎች አሏት። በዚች መጽሐፍ ስለ ላኢላሃ ኢለሏህ ምንነት እና ቅድመ ሁኔታዎቹ ፣ ስለ አርካኑል ኢማን እና ስለ አርካኑል ኢስላም ፣ ስለ ሶላት ፣ ስለ ውዱ ፣ ስለ ተውሂድና ክፍሎቹ ፣ ሙስሊሞች ሊላበሷቸው ስለሚገቡ ባህርያት ፣ ስለ ሽርክና ክፍሎቹ እንዲሁም ሌሎች አርዕስቶች በየምዕራፉ ተዳሰዋል። ለውቀት ጥማታችሁ መሰረት ሊሆን የሚችል እውቀት ለመቅሰም የንባብ ጅማሯችሁ እዚህ ይሁን።

Youth-Mission Iqra

ሒስኑል ሙስሊም(የሙስሊሞች ምሽግ)

free book gift

የሰው ልጅ ቀልቡ ይቆሽሻል ፣ ይዝጋል ፣ አለመረጋጋት ይገጥመዋል ፣ ስክነት ይጎለዋል። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ከእንዲህ አይነቱ በሽታ የምንፈወስበትን ስልት "አሏህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ(13:28)" ሲል አሳውቆናል።

ዚክር__አሏህን ማውሳት እና ማወደስ መረጋጋትን ለመጎናፀፍና ቀልብን ከቆሻሻ ለማፅዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ዚክር ለሙስሞች እጅግ በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

Youth-Mission Iqra

ጦሃራ ፣ ሶላት እና የቀብር ስነ-ስርአት አፈፃፀም

free book gift

ይህ መጽሐፍ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሶላት ያለውዱ ባዶ ነው ያሉበትን እንዲሁም ስሰግድ እንዳያችሁኝ አድርጋችሁ ስገዱ ይሉበትን ጉዳይ ይተነትናል። በዚች መፅሐፍ የገላ ትጥበትን ፣ የውዱ አደራረግን ፣ የተየሙም አደራረግን እና ጫማ ላይ እንዴት እንደሚታበስ በዝርዝር የሚማሩበት፤ ስለ ሶላትና ትሩፋቱ ፣ ስለ ሶላት አሰጋገድ ፣ ሶላትን ያለመስገድ ብያኔ ፣ ስለ ተውባ እና ስለ አጠቃላይ የቀብር ስነ-ስርአት ለማወቅ እና እውቀትዎን ለማዳበር ልዩ አስተዋፅኦ ይኖራታል።

Youth-Mission Iqra

የረመዷን ፆም

free book gift

የረመዷን ፆም ከአምስቱ የእስልምና ምሶሶዎች አንዱ ሲሆን በፆም ወቅት በሙስሊሞች ላይ ፍፁምነት ኢማንና ታማኝነት በጣም ጎልቶ ይታይባቸዋል። ፆመኛ ከመጠጥ ፣ ከምግብና ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች ሁሉ በሚታቀብበት ጊዜ አሏህ እንደሚቆጣጠረውና እንዲሚያየው ፍፁም እርግጠኛ ይሆናል።

በዚች መጽሐፍ ስለ ፆም ጥቅም ፣ ስነ-ስርአት ፣ ብያኔ ፣ ፆምን ስለሚያፈርሱ ነገሮች ፣ ስለ ሌሊት ሶላት ፣ ስለ ለይለትል ቀድርና ጥቅሙ ፣ ስለ ኢእቲካፍ ፣ ስለ ዘካተል ፊጥር ፣ ስለ ኢዶች ሶላትና ሌሎችም አስፈላጊ ነጥቦች ተዳሰውበታል።

Youth-Mission Iqra

እስልምና እና ክርስትና

free book gift

እስልምና እና ክርስትና ዛሬ በአለማችን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፉ ሃይማኖቶች ሲሆኑ እስልምና በተከታዮቹ ብዛት በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ሃይማኖት ነው። ሁለቱ ሃይማኖቶች ለረዥም ምዕተ አመታት በተለያዩ መስኮች ሲፎካከሩ ኖረዋል። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን የያንዳንዱ ሃይማኖት ተከታዮች ስለሌላኛው ሃይማኖት የሚያውቁት በጣም ጥቂቱን ብቻ ነው።

ይህ መጽሐፍ በሰባት ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም ትክክለኛነት ፣ እግዚአብሄር ፣ እየሱስ(ኢሳ) ፣ የእምነት መሰረቶች ፣ አምልኮ ፣ ስነምግባርና ህግ የሚሉ ጽንሰ ሃሳቦች ላይ ያላቸውን አቋም በተመለከተ በንፅፅራዊ መንገድ ለመመልከት የታለመ ነው። ሁሌም እንደሚባለው እውቀት ሃይል ነው። ማወቅ ካለማወቅ የተሻለ ነው። ይህ ንፅፅራዊ እውቀትም አንባቢው ለእራሱ ተስማሚ ሆኖ ሊያገኘው በሚችል መንገድ ሊጠቅመው ይችላል። በአሏህ ፍቃድ አዕምሮን ነፃ ልብን ክፍት አድርገው ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ ካነበቡት መላ ህይወትወን ሊለውጥ ይችላል።

Youth-Mission Iqra

ተጅዊድን ለማወቅ

free book gift

ቁርአን የጥበቦች ሁሉ መፍለቂያ ድንቅ እና ታላቅ መለኮታዊ መጽሐፍ ሲሆን ዘላለማዊ ተአምር የሆነ ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው። ይህን መለኮታዊ መጽሐፍ እያስተነተን ተረድተነው ለማንበብ ደግሞ ከቁርአን ጋር በሚኖረን ትስስር ልንላበሳቸው የሚገቡ ደንቦችና በስርአት ለማንበብ የሚያስችሉን ህጎች አሉ። ይህም የተጅዊድ ህግ ተብሎ ይጠራል። ለዚህም ነው አሏሁ አዘወጀል "ወረቲሊል ቁርአነ ተርቲላ" ያለን።

Youth-Mission Iqra

በራሂን የእስልምና እና የእምነት መሠረቶች ትንታኔ

free book gift

ይህ መጽሐፍ በኢስላም እምነትና መሠረት ዙርያ የተለያዩ ትምህርቶችን አጠር አድርጎ የያዘ መጽሐፍ ሲሆን ትምህርቶቹም በኢማን እና በኢስላም ምሰሶዎች ላይ ያተኮር ነው።

እነዚህ የኢማንና የኢስላም ምሰሶዎች ማንኛውም ሙስሊም በእምነቱ ስር እስካለ ድረስ ጠንቅቆ ሊያውቃቸው የሚገቡ መሠረታዊ ነገሮች ናቸው። ሆኖም እንዚህ መሰረታዊ ነገሮች ከቁርአንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን በማስደገፍ ተብራርተዋል።

Youth-Mission Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra