Snack's 1967
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

Iqra Iqra Note

የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የሶላት አሰጋገድ ሁኔታ

free book gift

የሰው ልጅ በትንሳኤ ቀን በመጀመሪያ የሚጠየቀው ስለ ሶላቱ ነው። እንዲሁም በሙእሚኖችና በኩፋሮች መካከል ያለ መለያ ሶላት ነው። ሶላት አንዱ የኢስላም ምሶሶ ሲሆን ልክ እንደሌሎቹ ኢባዳዎች ሊፈፀም የሚገባው የረሱልን ፈለግ በመከተል ነው። ይህን በተመለከተም ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ ብለዋል።

በዚች መጽሐፍ ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ሶላታቸውን እንዴት ይሰግዱ እንደነበር በጽሁፍና ምስልን በማስደገፍ አንድ ባንድ እንማራለን።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

ባሎቻቸውን ያስተማሩ ሙስሊም ሴቶች

free book gift

አላዋቂ ሙስሊሞችም ሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ የሴት መብት ጠበቆች ሙስሊም ሴቶች ጭቁኖች ፣ ኋላ ቀር ፣ በኢስላም ቦታ የሌላቸው አድርገው ያስባሉ።

የሴትን ልጅ ህይወት ከጨለማው ዘመን ያላቀቀ ፣ ሴቶች ከወንዶች ጋር ጦርሜዳ እንዲዘምቱ የፈቀደ ፣ እኩል ከወንዶች ጋር ሐዲሶችን እንዲያስተላልፉ ያደረገ ኢስላም እንደሆነ ቢያውቁስ። ህዝባቸውን ፣ ባላቸውን ፣ ልጆቻቸውን በማስተማር ይህን ትውልድ የቀረፁ ሴቶች እንዳሉ ቢረዱስ።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

ጥያቄዎቻችን እና የቁርአን መልሶች

free book gift

የሰው ልጅ በእለት ተዕለት ኑሮው በህሊናው ከሚመላለሱ ጥያቄዎች ወይም ማንኛውም ሰው ቆም ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ከሚገባው ጥያቄዎች አንዱ የመፈጠሬ አላማ ወይም ምድር ላይ የመኖሬ ሚስጥር ምን ድነው የሚለው ነው።

ለዚህና ከዚህ ጋር ተያያዥ ለሆኑ በርካታ ጥያቄዎችና የጥርጣሬ ምንጮች ዘላለማዊው ተአምር ቁርአን መልሶቻቸውን አስቀምጦልናል።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

የፆመኛ ሙስሊም መመሪያ

free book gift

የሰው ልጅ ያለ መመሪያና ደንብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ በመሆኑ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ የሰው ልጅ መመሪያ ያስፈልገዋል።

ሆኖም ፆመኛ ሙስሊም እንደሌሎቹ የእምነቱ ስርአት ሊከተላቸውና ሊተገብራቸው የሚገቡ መመሪያና ደንቦች እንደሚከተለው ተብራርተዋል።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

ተውባ በረመዷን

free book gift

ተውባ____አሏህ ለባሮቹ ከዋለው ትልቅ ችሮታ አንዱ ነው። በቅንነት ወደ እሱ ለተመለሱ ባሮቹ ወንጀሎቻቸውን በመማር መጥፎ ስራዎቻቸውን ወደ መልካም ስራ የሚቀይርላቸው መሆኑ ቃል የገባበት ነው።

በዛ ላይ ረመዷን ___የጀሃነም በሮች ተዘግተው የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ፣ ሸይጧን የሚታሰርበት ፣ ከሽ ወራቶች በላይ በላጭ የሆነችን ለሊት የያዝ ፣ ቀርአን የወረደበት ፣ የአሏህ እዝነት ያለሂሳብ የሚዘንብበት ነው። ለውጥን ካሰቡ አይቀር ይህኔ ነው።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

የጣኡት ትርጉም ማብራሪያ

free book gift

ይህ መጽሐፍ የተረጎምኩት ከኢማም ሙሐመድ ኢብን አብዱልወሃብ "ማዕነቱ ጣኡት" ከሚለው ፅሁፋቸውና ከዶ/ር ሙሐመድ ቢን አብዱ-ረህማን አልኩመይስ ማብራሪያ ሲሆን በውስጧም አራት ምዕራፎች አሏት።

  1. የጣኡት ትርጉምና ክፍሎቹ
  2. በሰው ልጆች ላይ የተደነገገው የመጀመሪያው ግዴታ
  3. በጣኡት መካድ የእምነት መስተካከል መሰረት ነው የሚሉ ሃሳቦች ተዳሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በየምዕራፍ መጨረሻ ማጠቃለያና እራሳችነን የምንፈትንባቸው መልመጃዎች ተካተዋል።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

የላኢላሃ ኢለሏህ ቅድመ ሁኔታዎች

free book gift

የላኢላሃ ኢለሏህ የምስክርነት ቃል የጀነት ቁልፍ ነው። ታዲያ ይህ የምስክርነት ቃል መሉ ይሆን ዘንድ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት። የቁርአን አናቅፅቶችን እና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ብናጠና የሸሃዳ ቅድመ ሁኔታዎች በቁጥር ስምንት ወይም ዘጠኝ እንደሆኑ እንረዳለን። ሆኖም ሁላችነም እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በህይወታችን የራሳችነን የእምነት ምስክርነት ያሟላን መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል። ነገሮች ከመበላሸታቸውና አቅጣጫ ስተው ከመሄዳቸው በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ለሟሟላት የቻልነውን ሁሉ ማድረግ አለብን።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

የኢማሙ ሻፊኢ ፊቅህ መሰረታዊ ነገሮች

free book gift

ይህ መጽሐፍ ስለ ኢስላም ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች እጥር ምጥን ባለ መልኩ እውቀት የሚያገኙበት እውቀት ያላቸውም ለመሸምደድ የሚያመች በመሆኑ እውቀታቸውን የበለጠ የሚያዳብሩበት ወይም ለማስተማር የሚረዳ ሆኖ ስላገኘሁት ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።

በዚህ መፅሐፍ ከተዳሰሱ አርዕስቶች መካከል የኢስላም ምንነት ፍች ፣ አምስቱ የኢስላም ህጎች ፣ ጦሃራ ፣ የቆሻሻ አይነቶችና የማስወገጃ መንገዶቻቸው ፣ ኢስቲንጃ ፣ ውዱዕ ፣ ጉሱል ፣ ተየሙም ፣ ሶላት ፣ አርካኑ ሶላት ፣ የኢድ ሶላቶች ፣ ዘካና ሃጅ ወ.ዘ.ተ አርዕስቶች ተዳሰውበታል። በየምዕራፉ የተነሳውን አርዕስት ምንያህል እንደተረዳነው እራሳችነን ለመፈተሽ ከእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ጥያቄዎች ተካተውበታል። አንብበን የምንጠቀምበትና ሌሎች እህት ወንድሞቻችነን የምንጠቅምበት ያድርግልን።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

ከአሏህ ሲሳይ ወይም ስንቅ የምናገኝባቸው መንገዶች

free book gift

ዘመኑ የውድድርና የሽቅድድም ዘመን በመሆኑ የሰው ልጅ ሩጫው ለዱንያና ዱንያ ለያዘችው ነገር ሆኗል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ሰዎች ስራ ማጣት ፣ በቂ ገቢ አለማግኘት ፣ እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት ነገር አለማግኘት ፣ ትዳር መስርተው የሚኖሩበት ወይም ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩበት በቂ ሲሳይ ማጣት ያስጨንቃቸዋል። ሆኖም ይህን ችግር ለማስወገድ በአሏህ መንገድ ላይ ሆነው ከመፈለግ ይልቅ ሃራም የሆኑ የለውጥ ጎዳናዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

በዚች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ እንዴት ቀናውን የአሏህ መንገድ ተከትለን ሲሳይ ማግኘት እንደምንችል ከቁርአንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን በማጣቀስ የተወሰኑ ጠቋሚ ነጥቦች ተዳሰዋል። መልካም ንባብ!

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

መልካም ፍፃሜ

free book gift

ሁሉም ሰው ህይወቱ መልካም ፍፃሜ ያገኝለት ዘንድ ይመኛል ያልማል። አብዛሃኛው ወጣቱ ክፍልም ነገን በተስፋ እየጠበቀ ወጣትነቱን ተደስቶበት በማሳለፍ ሃምሳዎቹና ስልሳዎቹ የእድሜ ክልል ላይ ወደ አሏህ እንደሚመለስብ ያስባል። ትልቁ ጥያቄ ግን ነገን ስለመኖርህ ዋስትናህ ምንድነው? ነገ የተቃና ሰው እንደምትሆን ምንድነው ማረጋገጫህ? የሚል ነው።

በዚች አነስተኛ መጽሐፍ የመልካም ፍፃሜ ምንነት ፣ ምልክቶቹ ፣ የመጥፎ ፍፃሜ ምንነትና ምልክቶቹ እንዲሁም ወጣቶች ላይ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችና ቁርአናዊ ግሳፄዎች ተዳሰውበታል ያንብቡት!

Youth-Mission Youth-Mission Iqra

ወጣቶች ሆይ! ዛሬውኑ ወደ አሏህ እንመለስ!

free book gift

ወጣቶች ደስታን ለማጣጣም ወይም ከጎደኞቻቸው ጋር ላለመለያየት ወይም ደግሞ ዱንያዊ ኑሯቸውን ለማቃናት ሲሉ ከአሏህ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያቋርጣሉ። አሉ የተባሉ ሃራም ነገሮችንም ይሰራሉ። የሚፈልጉትን ነገር በሃላል መንገድ ማግኘት ሲችሉ አሏህን በማመፅ ላይ ይፈልጋሉ።

ወቅቱ ወጣቱ ክፍል ለወጣትነት ጊዜው ትኩረት የማይሰጥበት ፣ ለዲኑ ግዴለሽ የሆነበት ፣ ከእውቀት ይልቅ አሉቧልታን ያስቀደመበት ፣ ከመስጊድ የራቀበት ፣ አዋዋሉ የማያምርበት ፣ ለጊዜ ዋጋ የማይሰጥበት የድንቁርና ጊዜ በመሆኑ ይችን ፅሁፍ ልፅፍ ወደድኩ አውርደው ያንብቧት!

Youth-Mission Youth-Mission Iqrafree book gift

ረመዷን 11 ወር ሙሉ ስሜቱንና መጥፎ ምኞቱን ተከትሎ ለኖረ ሰው ሁሉ ልጎም ፣ ለመልካም ሰሪዎች በረካ ሲሆን አዲስ የለውጥ ቤዛ ነው። ታዲያ ፆምን ፆም የሚያደርገው የምግብና የመጠጥ ተአቅቦ ብቻ ሳይሆን አሏህ የከለከላቸውን ነገሮች ሁሉ በመከልከል ያዘዛቸውን ነገሮች በመታዘዝ መልካም ነገሮችን መስራት ነው። ፆም.....በእናንተ ላይ ተደነገገ አሏህን ትፈሩ ዘንድ(2:183)።

ይህን ላደረገ ሰው ሲሳዩ በዱንያም በአሂራም ይሰፋል፤ እንከኖቹን አስወግዶ እራሱን በኢስላም ድስፕሊን በማነፅ የለውጥ ምሳሌ መሆን ይችላል። በረመዷን ወቅት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከሌላው ጊዜ በበለጠ በኢባዳ ይተጉ ነበር።

Youth-Mission Youth-Mission Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
9256

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ