=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ወራት አልፎ ወራት ሲተካ ተወዳጅ እና ታላቅ የሆነው የሚልዮኖች እንግዳ ሸኽሩ ረመዷን በድጋሜ ብቅ ይላል። በዚህ ወቅት ሙስሊሞች እንግዳውን ሲቀበሉ ውስጣቸው በሐሴት(በደስታ) ይሞላል። ላለመደው ሰው ሙስሊሞች ከዚህ በፊት ተገናኝተውት የማያውቁ ሊመስለው ይችላል።....Read more
የረመዷ ወር በጣም ርህሩህ ቸር የሆነው አምላካችን አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ወደ እሱ እንድንቀርብ ፣ ከርሱ ጋር ያለንን ትስስር እንድናጠብቅ ፣ ምህረትን እንድንጠይቅ ፣ ለመጭው አለም ስንቅ እንድንይዝ ፣ ስብዕናችነን እንድናስተካክል ፣ አላማችነን እንድንቀርፅ የሰጠን እድል....Read more
ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው። የተውባ የቃል በቃል ትርጉሙ መመለስ ማለት ሲሆን አሏህን ወደ ማስታዋስ እና ወደ መታዘዝ መምጣት ማለትም ነው።
ተውባ በማድረግ ሐጢያተኞች ከሐጢያታቸው ይማራሉ። ምክኒያቱም አሏህ(ሱ.ወ.ተ) እጅግ በጠም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ መሃሪ ነውና።....Read more
መስተካከልን አስበን ወደ አሏህ ለመመለስ ከቆረጥን አሏህ በባሮቹ ላይ አይጨክንም። የውሸት ኑሮን አንኑር ወደ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ብንመለስ ነው የሚሻለው።
እንስተካከል ነገሮች ሁሉ ይስተካከሉልናል። ከህይወት ወከባ እናርፋለን፤ ወደ ማይቀረው አለም ስንሄድ አንፈራም እንደፍራለን። መስተካከል የአሏህ እዝነት ነው። ጥመት ደግሞ የእሱ ቁጣ ነው።....Read more
በሱረቱ ተውባ መካከለኛዋ አያ ላይ አሏህ በተውበት ወደ እሱ ከተመለስን መጥፎ ስራዎቻችነን በመልካም ሊቀይርልን ቃል ገብቷል።
=<({አል-ቁርአን 25:70})>=
(70) እነዚያ የተፀፀቱት ፣ ያመኑትና መልካም ስራን የሰሩት ሲቀሩ። ለነሱም አሏህ መጥፎ ስራዎቻቸውን ሃጢያታቸውን በመልካም ስራ ይቀይርላቸዋል። አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው።....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|