=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ምን ያማረ ስም ነው ጣፋጭ
ይዞጭልጥ የሚል ልብ መሳጭ
በአንተነትህ የተጥራራህ
ከፍጥረታት የተብቃቃህ
ሰማይና ምድርን የዘረጋህ
ምስጋና ሁሉ የሚገባህ
አጋዥ የለህ አማካሪ
ያሻህን ሁሉ ሰሪ
አስተካካይ አሳማሪ
ራስህን የቻልክ ተብቃቂ
ይፋ ድብቅ ሁሉ አዋቂ
ህይወት ሰጭ ጥበበኛ
ስለእውነት ፈራጅ ዳኛ....Read more
ለምን ይሆን ጥገኝነት
የሰው ድጋፍ ፈላፊነት
አንድ ስንዝር ኑ ወደኔ
ጥሩኝ እንጂ እቀበላለሁ እኔ
እያለ ሲጣራ በግልፅ በይፋ
እንዳልሰማን ሆንን ብለን ጀሮ ዳባ....Read more
ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤
መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤
የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤
እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤
የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤
አሏህ አልፈጠረም አንዳች ነገር፤
እንዲኖር እንጂ በሱ ትዕዛዝ ስር፤....Read more
ለከፊሉ እስር ቤት ለቀሪውም ገነት፤
ከፈጣሪዋ ዘንድ እንስ ያለች መሬት፤
ዱንያ ዋጋ ቢሷ ከህልም ያላለፈች፤
በእቅድ በምኞት በባዶ የተሞላች፤
እኛንም ጠራርጋ ገደል ይዛን ገባች፤
አይይቀሬውን ጉዳይ ሞትን አስረስታ፤
በብልጭልጭ ነገር ዳንኪራ አስመትታ፤....Read more
ውበትሽ ነው ላንቺ ክብር መጠበቂያ፤
ወንድ ላይሳሳት ውበት መደበቂያ፤
ቀልቡ እንዳይሰበር ልቡ እንዳይሸፍት፤
እባክሽ ልበሽው ጥቅም አለው እህት፤
አይቀርም ቂያማ አብረሽ መጠየቅሽ፤
በሠራሽው ጥፋት አብረሽ መቀጣትሽ፤....Read more
ጠፍቶብኝ የአሏህ ሰፊ ችሮታ
ትናንትን የኖርኩት ሆነብኝ ብዥታ።
መጭውንም ጊዜ ሳላውቀው
መኖሬንም ቀጠልኩ ዛሬ ነገ እንደሚል ተስፋ እንደቆረጠ ሰው።
ደስታን ለማጣጣም ስሰራ በርትቼ፤
የተፈጠርኩበትን አላማ ረስቼ፤
ዛሬን ስኖር በኩራት በዝና፤....Read more
እናት አለም ክብሬ እማየ አንደቤቴ፤
የመኖሬ ዋስትና የዘጠኝ ወር ቤቴ፤
በደምሽ ታንፃ መልካሟ ሂወቴ፤
እኔ ስስቅ ስቀሽ ስከፋ ተከፍተሽ፤
ሲርበኝ ተርበሽ
ሲጠማኝ ተጠምተሽ፤
በመልካሙ ምኞት መልካሙን አስበሽ፤
የወደፊት ተስፋየን ሂወቴን አብርተሽ፤....Read more
የሰው ልጅ ስሜቱን ከላዩ ሲያነግስ፤
ለአሄራ መስራቱን ትቶ ለጀሃነም ሲደግስ፤
ሃራምን በመስራት ምድርን ሲያድበሰብስ፤
ያሻውን ሲጠጣ ያሻውን ሲበላ፤
ያማረውን ሲወድ ሲፈልግ ሲጠላ፤
ሃራምን በመሥራት መልካምን ሲያጥላላ፤....Read more
በጣም የምወደው ታናሹ ወንድሜ፤
ይፈካከረኛል ሳይቀር በህመሜ፤
ስበላ ከበላ ሳቆምም ከበቃው፤
ሀሙስ ሰኞን ፁሜ ፆምን ላስለምደው፤
ረመዷን ሲመጣ ምንም እንዳይከብደው፤
አርሰናል ስለው ማንቼ ካለኝማ፤
ለአምስት ወቅት ሰላት ምንም ሳላቅማማ፤
ልቁም ይየኝ እስኪ እሱም ይቁማ፤
እንዳይጨነቅብኝ በየውመል ቂያማ፤
ፀጉሬን ሳሳድግ ፀጉሩን ካሳደገ፤
ሱሪየን ሳስረዝም እሱም ካስረዘመ እኔን በመከተል ሁሉን ካደረገ፤
እስኪ ቁርአን ልቅራ፤
እሱም እንዲቀራ፤
እንዲሰለፍልኝ ከአዋቂዎች ጐራ፤....Read more
ድቅድቁን ጨለማ ከላይ ሰመለከት፤
ከርቀት አየሁኝ የካንፓስ ከዋክብት፤
ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤
አለው ልዩ ውበት ከርቀት ይስባል፤
ውስጤንም ጠየኩት ማናት ያቺ ኮከብ፤
በካምፓስ አድማስ ላይ የለበሰች ጅልባብ፤
ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤
አለው ልዩ መስህብ ከርቀት ይስባል፤....Read more
እንዲያ ተቸግረን፤
ፊት እንዳልገረፈን፤
ጥፈን እንዳለበስን፤
ጭረን እንዳልበላን፤
ከሰው እኩል ሆነን፤
መውጣት እንዳልከጀልን፤
ቀን እንዳልናፈቀን፤
ጊዜ እንዳልጠበቅን፤....Read more
ከክፉ የራቀ
ለኸይር የታጠቀ
ለአኺራ የሚተጋ
ለኸቲማው የሚሰጋ
በቀደር ያመነ
በአደጋ የሰከነ
የኔ ብቻ የማይል
ድክመቱን የሚቀበል
ታላቁን አክባሪ
ለታናሹ ራሪ
ፈርዱን ቸል ያላለ
ከሱናውም ያለ
ንግግሩ ተግባር
ህይወቱ ቁምነገር....Read more
ልቡ ጥሩ አሳቢ ምላሱ የገራ፤
ብዙ የሚሠማ ትንሽ የሚያወራ፤
ፊቱ በተዋዱዕ በኢማን ያበራ፤
ፈገግታው የሚስብ ከሩቅ የሚጣራ፤
በፈርዱ የቆመ ከሱናውም ያለ፤
ደበረኝ ሰለቸኝ ደከመኝ ያላለ፤
ለረጅሙ ጉዞ ጥሩን የሰነቀ፤
ለማይቀረው ዓለም መሄዱን ያወቀ፤
ፀባዩ የሚጥም ወግ አመሉ ሸጋ፤
እኔስ ሰው ጠፍቶኛል እንሂድ ፍለጋ፤....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|