=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
• አደብ__ኢስላማዊ ባህሪ
• አቂዳ__እምነት
• አድል__ፍትህ/መልካም ባህሪ
• አህካም__ህግ/ትዕዛዝ
የኢስላምን ህግ መሠረት በማድረግ 5 ትዕዛዞች አሉ
1) ዋጅብ__ግዴታ
2) ሙስተሃብ__የተወደደ
3) ሐራም__የተከለከለ
4) መክሩህ__የተጠላ
5) ሀላል__የተፈቀደ/ህጋዊ
• አሂራ__መጭው አለም
• ቢድአ__ከቁርአን ፣ ከሐዲስ እና ከሸሪአ መሠረት የሌለው እንዲሁም በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ማንኛውም የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ከራሳችን ስሜትና ፍልስፍና በመነሳት በዲነል ኢስላም ላይ ያልነበሩ ነገሮችን መጨመር ወይም መቀነስ ነው።
__ቢድአ ማለት በኢስላም ላይ መፈላሰፍ ነው።
• ዶኢፍ__ደካማ
የአንድ ሐዲስ የተላለፈበትን ሰንሰለት እና በእምነቱና በተግባሩ ሙሉ ስምምነት የሌለው ሐዲስ መገለጫ ነው።
• ፊትና__ፈተና
• ፊጥራ__ተፈጥሯዊ/ተፈጥሮ/የተፈጥሮ
• ሐዲያ__ስጦታ
• ሀጅ__አንዱ የእስልምና ምሰሶ ነው።
• ሐሰድ__ምቀኝነት
• ሐያእ__ይሉኝታ
• ሂጅራ__ስደት
• ሂክማ__ጥበብ
• ሁክም/አህካም__ድንጋጌ/ፍርድ
• ኢባዳ__አሏህን የመገዛት ተግባር/የአምልኮት ተግባር
• የኢባዳ (የአምልኮት ተግባር) ሁለት ሁኔታዎች አሉት
1) ለአሏህ ቅን መሆን
2) ለአሏህ መልእክተኛ መታዘዝ(ሱናውን መከተል)
=>ከኢባዳዎች መካከል ሶላት ፣ ዘካት ፣ ፆም ወ.ዘ.ተ የአሏህ ፍራቻ በልብ ውስጥ መኖር እርዳታውንና ምህረቱን መሻት
• ኢህሳን__የአንድ ኢባዳ (ስራ) ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ
__አንድን ኢባዳ ስትሰራ ወይም አሏህን ስትገዛ አሏህን እንደምታየው ሁነህ መገዛት ይህን ማድረግ ከቻልክ አሏህ እንደሚያይህ ሆነህ መገዛት ወይም መስራት ማለት ነው።
• ኢጅቲሃድ__የሙስሊም ሊቃውንቶች መንፈሳዊ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያደርጉት አእምሯዊ ጥረት
• ኢኽላስ__ጥርት ያለ ቅንነት
• ኢልም__እውቀት
• ኢሻራት__የመጨረሻው ቀን ምልክቶች
• ጃሚእ__ሰፋ ያለና ሁሉን አቀፍ የሐዲስ ማጣቀሻ መፅሐፍ
• ጂሃድ__በአሏህ (ሱ.ወ) መንገድ ጥረት ወይም ትግል ማድረግ
• ከራም__ለጋስነት/ቸርነት
• ኪበር/ኪብር__የተሳሳተ(የውሸት) ኩራት
• ኪታብ__መፅሐፍ
• ሁጥባ__ስብከት
• ኩፍር__የአሏህን አምላክነት መካድ
• ሙጃሂድ__በአሏህ መንገድ ጥረት ወይም ትግል የሚያደርግ
• መውዱእ__የተፈበረከ በተለይ ለሐዲስ
• ሙተፈቁን አለይህ__ስምምነት የተደረሰበት/በቡሐሪይ እና በሙስሊም የተላለፈ ማንኛውም ሐዲስ
• ሙወጢር__ቀጣይነት ያለው/በተለያየ ጊዜ በብዙ ሰዎች የተዘገበ ሐዲስ
• ቀደር__መጥፎም ሆነ ጥሩ የሚከሰተው አሏህ የደነገገው ነው ብሎ ማመን
• ረህማ__ምህረት/እዝነት
• ሪፋቅ__መልካምነት/ደግነት
• ሶብር__ራስን መቆጣጠር/ታጋሽነት
• ሶሂህ__ትክክለኛና ምንም እንከን ወይም ደካማ ላልሆነ ሐዲስ የተሰጠ ስም ነው።
• ሰውም__ፆም
• ሸሂድ__ራሱን በአሏህ መንገድ የሰዋ
• ሽርክ__ለአሏህ አጋር ወይም ባላንጣን ማበጀት/ማጋራት
• ሽርክ(ማጋራት) ሶስት ክፍሎች አሉት
1) አሽርኩል አክበር__ትልቁ ማጋራት
2) አሽርኩል አስገር__ትንሹ ማጋራት
3) አሽርኩል ኸፊይ__ድብቁ ማጋራት
• አሽርኩል አክበር__ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር ላይ ማመን(ማምለክ)
=>አሏህ በሽርክ ላይ የሞተን ሰው አይምርም መልካም ስራውንም አይቀበለውም እናም ከኢስላም ውጭ ይሆናል
• ሽርኩል አስገር__ትንሹ ማጋራት
አሏህን ለማስደሰት ተብሎ ሳይሆን ዝናን ክብርን እና ምስጋናን ከሰዎች ዘንድ ለማግኘት ተብሎ የሚሰራ የአምልኮት ተግባር ነው።
የዚህ አይነቱ ማጋራት አንድን ሰው ከኢስላም ውጭ አያደርገውም
• አሽርኩል ኸፊይ__ይህ ማጋራት አሏህ በደነገጋቸው ሁኔታዎች ላይ አለመርካት ወይም ቅርመሰኘት ነው።
• ሲራጥ__ማለት በመሠረቱ መንገድ ማለት ሲሆን ሰዎች በፍርዱ ቀን የሚያልፉበት በጀሃነም እሳት አግድም የሚቀመጥ ድልድይ ማለት ነው። ይህም እንደጐራዴ የሰላ እና ከፀጉር በላይም የቀጠነ መሆኑ ተገልፇል።
• ሱፍህ__በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መስጅድ ውስጥ የተመሠረተ የመጀመሪያው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ
• ጣጉኡት__ከአሏህ ውጭ ያለ ማንኛውም የሚመለክ ነገር ሁሉ ጣጉኡት(ጣኦት) ነው።
• ተስፊያህ__ማፅዳት
• ተውሂድ__አሏህ በራሱ የገለፃቸውን ባህሪያቶቹን እና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የገለፇቸውን የአሏህ ባህሪያቶች ማረጋገጥና አሏህ ሊመለክ የሚገባው ብቸኛ አምላክ መሆኑን ማወጅ ማለት ነው።
ተውሂድ ሶስት ክፍሎች አሉት
1) ተውሂድ አሩቡብያህ
2) ተውሂዱ አል-ኡሉሂያ
3) ተውሂድ አል-አስማኡ ወሲፋት
• ተቅሊድ__ጭፍን እምነት/በጭፍን መከተል
• ተዋዱእ__ራስን ዝቅ ማድረግ/መተናነስ
• ተወኩል__በአሏህ መመካት/መወከል
• ዑለማ__አሊም
• ዑለማህ__አሊሞች
• ኡማ__ሙስሊም ማህበረሰብ
• ዘካህ__አንዱ የኢስላም ምሰሶ ሲሆን ፍቹም ለድሆች ምፅዋት መስጠት ማለት ነው።
• ሪባ__አራጣ
• አጅር__ምንዳ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|