=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ኢባዳ የሚለው ቃል ሸሪአዊ ፍቹ አሏህ የሚወደው ማንኛውም በግልፅም ይሁን በድብቅ የሚሰራን፤ በንግግር እና በተግባር የሚገልፅን ስራ ሁሉ የሚያጠቃል ቃል ነው።
ታላቁ ሙፈሲር እና የአልቢዳያ ወኒሃያ አዘጋጅ ኢብን ከሲር የኢባዳን ትርጉም ሲያስቀምጡ ኢባዳ ማለት አሏህ ያዘዘውን ነገር በመስራት የከለከለውን ነገር በመከልከል ለእሱ ታዛዥ መሆን ነው። የኢስላም ትርጉም ኢስቲስላም ሲሆን ኢስቲስላም ማለት በሙሉ ታዛዥነት እና መተናነስ ለአሏህ እጅ መስጠት ማለት ነው ብለዋል።....Read More
ሸይጧን የጅኖች ወይም የአጋንት አንዱ አካል ሲሆን የራሳቸው የሆነ አለም ወይም መኖሪያ አላቸው። እራሳቸውን ከሰው ልጅ እይታ ከመሰወር ብቃት ጋር የተፈጠሩም ናቸው። ሸይጧን እራሱን እንደ ሰው ልጆች ሁሉ የሚያበዛ ሲሆን የራሱ የሆኑም ዘሮች አሉት።
ሸይጧን ሰለባዎቹን የሚቀርብበት መንገድ እንደ ሰው ልጆች ፍላጐትና ዝንባሌ ይለያያል። ኡለማዎችን በኡለማዎች ያጠቃል መሃይሞችን በመሃይማን ያጠቃል።....Read More
ልዑል ሃያል ስለሆነው አሏህ ያለ እውቀት ስለ እሱ መናገር የከፋ የአሏህን ቅጣት የሚያመጣ ሲሆን ከወንጀሎችም ሁሉ የከፋ ወንጀል ነው። በዚህም ምክኒያት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሁነን ቢሆን እንኳ ያለ እውቀት ስለ አሏህ መናገር አይኖርብንም። አሏሁ አዘወጀል በሱረቱል አዕራፍ ከሌሎች ከባባድ ወንጀሎች ጋር እያወዳደረ የወንጀሉን ከባድነት ገልፆልናል።....Read More
ቁርአን ለማንበብ ግልፅ የሆነ ልንስራራበት እና ልናስተነትንበት የሚገባ ሲሆን ለሰው ልጆች በረካ የሆነ መለኮታዊ መጽሐፍ ነው።
በሙስሊም እንደተዘገበው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-ከአሏህ ቤት የአሏህን መጽሐፍ ለመቅራትና በአንድላይ ሊያጠኑት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም የመንፈስ እርጋታና ምህረት አካቧቸው ፣ መላኢካዎች ከበዋቸውና አሏህ ከነሱ ጋር ሆኖ ቢሆን እንጂ ብለዋል።....Read More
ሸይጧን ጭስ አልባ ከሆነ እሳት የተፈጠረ ሲሆን መላኢካ ባይሆንም ለአሏህ በነበረው ታዛዥነት ግን በጀነት ከነሱ መካከል ነበር። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) አደም(ዐ.ሰ) በፈጠረ ጊዜ በጀነት ያሉ ሁሉ ከአደም(ዐ.ሰ) ፊት ለፊት ይሰግዱ ዘንድ አዘዛቸው። ነገር ግን ሸይጧን በእብሪተኝነት እና በኩራት አሻፈረኝ አለ።
አሏህም ሸይጧንን ረግሞት ከጀነት አባረረው። ሆኖም ግን ሰዎችን የሚያጠምበትን እድል ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ፤ አሏህም የጠየቀውን ነገር ሰጠው።....Read More
ኡለማዎች የአንድን ሰው ኢስላም ዋጋ የሚያሰጡ ብዙ ነገሮች እንዳሉ የጠቀሱ ቢሆንም የሚከተሉት 10 ነገሮች የተለመዱ ናቸው።
1 በአሏህ ላይ ማሻረክ
2 በሰዎች እና በአሏህ መካከል አስታራቂን(ባላንጣን) ማበጀት
3 አሏህን በኢባዳ የሚያሻርኩትን እንደ ከሐዲ አለመቁጠር ፣ ክህደታቸውን መጠራጠር ወይም እምነታቸው ትክክል እንደሆነ ማሰብ....Read more
ኢስላምን አስመልክቶ አንድ ሰው በቅድሚያ ሊያውቀውና በግልፅ ሊረዳው የሚገባው ነገር ኢስላም የሚለው ቃል ትርጉሙ ራሱ ምን ማለት እንደሆነ ነው። ክርስትና ከእየሱስ፤ ቡድሂዝም ከጉተማ ቡድሃ፤ ከኮንፊሽየስ እንዲሁም ማርክሲዝም ከካርል ማርክስ ስያሜያቸውን እንዳገኙ አይነት የእስልምና ሃይማኖት ስሙን ከግለሰብ ስም አልወሰደም። እንደ አይሁዳ ከይሁዳ ጐሳና እንደ ሕንዱይዝም ከህንዱ መጠሪያ ስሙን አላገኘም። ኢስላም የአሏህ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም መጠሪያ ስሙ የአሏህን ሃይማኖት ማእከላዊ መርህ ለአሏህ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መገዛትንና ማደርን....Read More
አሏህ የማንኛውም ነገር ፈጣሪ ፣ ሰጭ ፣ ነሽ ሲሆን አምልኮት ለእሱ ብቻ የሚገባ፤ እሱም ውብና ሙሉ የሆኑ ስምና ባህርያቶች ያሉት ጌታ ነው።
ልጆች አሏህ በዙርያችን የምናያቸው እና የማናያቸው ፍጥረቶች ጌታ ነው። ለምሳሌ የመላኢካዎች ፣ የጅኖች ፣ የሰዎች ፈጣሪ ነው። አሏህ መላኢካዎችን ከብርሃን የፈጠረ፤ ጅኖችን ከዕሳት የፈጠረ ጌታ ነው።....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|