=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
💬 ኢማሙ ሻፊእይ(ረሂመሁሏህ) ከቁርአን ፣ ከሐዲስ ወይም ከሱሐቦቻቸው ንግግር መሰረት የሌለው ማንኛውም የኢባዳ ተግባር ቢድአ ነው ብለዋል።
💬 ኢብን አልጀውዚ(ረሂመሁሏህ) ቢድአ ማለት በነብዩ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እና በሶሃቦቻቸው ዘመን ያልነበረ ከጊዜ በኋላ የተፈጠረ ማንኛውም የኢባዳ አይነት ቢድአ ነው ብለዋል።
💬 ኢብኑ ረጀብ(ረሂመሁሏህ) ከሸሪአ መሠረት የሌለው ማንኛውም የኢባዳ አይነት ቢድአ ነው ብለዋል።
የቢድአን ፍች ለማጠቃለል ያህል ቢድአ ማለት ከቁርአን ፣ ከሐዲስ ፣ ከሸሪአ መሰረት የሌለው እና በረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ወይም ያላደረጉት የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ሁሉ የሚያጠቃልል እና ከራሳችን ፍልስፍናና ስሜት በመነሳት ያልነበሩ ነገሮችን በዲነል ኢስላም ላይ መጨመር ነው።
ባጠቃላይ ሁሉም የኢባዳ ተግባሮች ሊሰሩ የሚገባቸው ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በሰሩባቸው መንገዶች ብቻና ብቻ ነው። ይህም የሚከተሉትን ስድስት ሁኔታዎች ያሟላ መሆን ይኖርበታል።
ያለበለዚያ ስራችን ውድቅና በራሳችን ጊዜ የምንጠምበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው። ስለዚህ መወሊድን ማክበር በራሱ ቢድአ ፣ ጥመት ነው። ምክኒያቱም በሸሪአ አልተደነገገም ፣ ሶሃቦች እንዲያከብሩ አልታዘዙምና።
ስለዚህ አንድ ሰው ከሐጅ ቡኋላ በግመል ወይም በፍየል ፈንታ እንደ መሦዋዕት አድርጐ ፈረስ ቢያርድ ተቀባይነት አይኖረውም።
ስለዚህ አንድ ሰው በዙሁር ሶላት አራት ረከአ በመስገድ ፈንታ ሁለት ረከአ ጨምሮ ባጠቃላይ ስድስት ረከአ ቢሰግድ ተቀባይነት አይኖረውም። ድርጊቱም ጠማማ ተግባር ነው።
ስለዚህ አንድ ሰው ውዱእ ሲያደርግ እጁን በመታጠብ ፈንታ እግሩን በማጠብ ቢጀምር ተቀባይነት አይኖረውም።
ስለዚህ ፀሀይ ስትጠልቅ የዙሁር ሶላትን መስገድ ተቀባይነት አይኖረውም።
አንድን ኢባዳ በረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ለመስራት ኢባዳው በዝርዝር ነገሮች ፣ በመጠን ፣ በቦታ ፣ በሰአትና በምን አይነት መንገድ መከወን እንዳለበት ከሸሪአ ድንጋጌዎች ጋር ሊስማማ ይገባል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|