XtGem Forum catalog
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

:☀:..•"ღ ተውባ ღ"•:☀:


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው።

የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው። የተውባ የቃል በቃል ትርጉሙ መመለስ ማለት ሲሆን አሏህን ወደ ማስታዋስ እና ወደ መታዘዝ መምጣት ማለትም ነው።

ተውባ በማድረግ ሐጢያተኞች ከሐጢያታቸው ይማራሉ። ምክኒያቱም አሏህ(ሱ.ወ.ተ) እጅግ በጠም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ መሃሪ ነውና።

አሏህ ከኛ ሙሉእነትን አይጠብቅም፤ ከኛ የሚጠብቀው ስተት በሰራን ወቅት ከአመፀኝነት ፣ ከወንጀለኝነት እና ካለመታዘዝ ወጥተን አሏህን ያዘዘንን ነገር ሁሉ ለመታዘዝ ፣ የከለከለንን ሁሉ ለመከልከል በተውባ ወደ እርሱ መመለስ ብቻ ነው። ነገርግን ለብዙ ጊዜ ወንጀል እየሰራን፤ ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ምህረትና ከለላን ካልሻትን ምህረቱንም ካለመን ነፍሳችንም መወንጀሏን ትቀጥላለች፤ በወንጀላችነም ብዛትና ፅናት ትበሰብሳለች፤ መመለሻችንም የከፋ ይሆናልና ይህ ከመከሰቱ በፊት የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ፍራቻ በልባችን ውስጥ ዛሬውኑ መዝራት ይኖርብናል።

- መወንጀልን ሆንብለን ማቆም አለብን

- በወንጀላችን ላይ ልባዊ የሆነ ፀፀት ይኑረን

- እራሳችነን ወንጀል ላይ ከሚጥሉ ነገሮች ሁሉ እናርቅ

:☀:ሁለት የበደል አይነቶች:☀:


1) በአሏህ(ሱ.ወ.ተ) እና በባሪያው መካከል ያለ
ለምሳሌ:- ሽርክ ፣ ዚና ፣ ግድያ ፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ወ.ዘ.ተ

2) በሌሎች ሰዎች ላይ ያደረስነው መጥፎ ስራ
ለምሳሌ:- ሐሜት ፣ መስረቅ ፣ ዋሽቶ ማጣላት ወ.ዘ.ተ

በሌላ ሰው ላይ የሰራ ነው ወንጀል ካለ ያን ወንጀል ወይም ስህተት መጠገን አለብን። መጥፎ ነገሮች የተናገርነው ፣ ያማነው ፣ የሰረቅ ነው ወይም በሌላ መንገድ የጐዳነው ሰው ካለ አውፍ እንዲለን ደጋግመን መጠየቅ ወይም ሐቁን መመለስ ይኖርብናል።

በደል ወይም ወንጀል ከሰራንና በሰራ ነው ነገር ላይ ከተፀፀትን ወንጀላችን ጉምን አልፎ ሰማይን የሚነካ ቢሆን እንኴ ከልባችን ከቶበትን አሏህ ይምረናል። ከዚህም በላይ አሏህ መጥፎ ስራዎቻችነን በመልካም ነገር ሊቀይርልን ቃል ገብቶልናል። ይህም በአሏህና በባሪያው መካከል ላለ በደል ወይም ወንጀል ነው።


=<({አል-ቁርአን 25 : 70})>=

{70} እነዚያ የተፀፀቱት ፣ ያመኑትና መልካም ስራን የሰሩት ሲቀሩ። ለነሱም አሏህ መጥፎ ስራዎቻቸውን ሃጢያታቸውን በመልካም ስራ ይቀይርላቸዋል። አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው።

በሌሎች ሰዎች ላይ ላደረስነው በደል አሏህ አያገባውም። ስለዚህ እነሱ ከልባቸው አውፍ እንዲሉን መጠየቅ ወይም ሃቃቸውን መክፈል ይኖርብናል።

ሆኖም ስራችነን ፣ ንግግራችነን እና ልባችነን ለማፅዳትና አሏህን ወደ መታዘዝ ጐዳና ለመምጣት ተውባን እስቲግፋር ማዘውተር ይኖርብናል።


1349

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ